ቻይና ለአፍሪካ አገራት የማሰቃያ መሳሪያዎችን እንደምትሸጥ አምነስቲ ገለጸ

MaYz-eE2kUEjaGB28PhZZAL45W1HIAYY034usCOSvK2w
መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ 130 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ለአፍሪካ መሪዎች በእስር ቤት ጥቅም ላይ የሚሆኑ የማሰቃያ መሳሪያዎችን ይሸጣሉ።
የኤልክትሪክ ንዝረት ያላቸው ከብረት የተሰሩ ሹል ዱላዎችና ሌሎችም የማሰቃያ መሳሪያዎች ለአፍሪካ እና ለእስያ አገራት መሸጣቸው በአህጉራቱ ውስጥ የሚታየውን ሰብአዊ መብት እረገጣ አባብሶታል። በአለም ላይ ስለት ያላቸውን የንዝረት
ብረቶችን የምታመርተው ቻይና ብቻ መሆኗን የጠቀሰው አምነስቲ፣ ፖሊሶች በእስረኞች የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ላይ በማሳረፍ ስቃይ እኢነደሚፈጽሙ አጋልጧል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቻይና የማሰቃያ መሳሪያዎችን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ወደ ሚፈጽሙ አገራት እንዳትልክ ግፊት እንዲደረግ ጠይቋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: