መብታችን ይከበር ማለት አሸባሪነት አይደለም !!

weareone_respectናትናኤል በርሔ ( ኖርዌይ )

ኢትዮጵያ 94.1 ሚልዮን በአፍሪካ ከናይጄሪያ ቀጣላ ህዝብ የምኖርባት በ2ኛ ደረጃነት የምትገኝ አገር ናት።የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው አገሪቱ ያለባት የጠቅላላ የብድር መጠን 20 ዶላር ደርሷል።መንግስት ከውጭ አለማት የመበደር አቅሙን እያስተዋለና እያገናዘብ ካልሄደ የድብር መጠንንዋ ከዚህ በላቀ ሊሆን ይችላል።ለአንድ አገር እድገት አስተማማኝ ነው የሚባለው የመትልከው ምርት ከምትበደረው ብድር የበለጠ መሆን አለበት ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ያብራራሉ።ይህንንም ለማድረግ አስተማማኝ የፋይናንስ ሪፖርት ግልፅነት፣ወጥነት በጣም ጠቋሚ ነው።ተዓማኒነት ያለው መረጃም መኖሩ ግድ ይላል።ላለፉት ሁለት አስር አመታት አንድ የቴሌቪዥን ማሰራጫ ፣በብዛት የመንግስት ልሳን የሆኑ ጋዜጦች መፅሄቶች፣ጥራት የጎደለው አንድ የቴሌኮምንኬሽን መስሪያ ቤት እሱም የግለሰቦችን መብት ለመሠለል የገዢውን መንግስት ለማገልገል የተቀመጠ መንግስታዊ ተቋም ነው።በቅርቡ 2014 የወጣ ዋሽንግተን ፖስት ያተመው አለም አቀፍ ጥናት እንደሚያመለክተው 11 % በላይ አድጋለሁ የምትል አገር ህዝቧ98.7 % ኢንተርኔት የመጠቀም መጠኑ አነስተኛ መሆኑ የእድገቱ መጠን የቱ ላይ እንደሆነ ያጠያይቃል።
የኢትዮጵያ መንግስት በ1988፣1992፣1997 ታሪካዊ ምርጫ እና 2002 ዓም አገር አቀፍ የምርጫ እንቅስቃሴ አድርጎ በሁሉም የምርጫ ዘመን በዝረራ ቢወጣም የስልጣን ጥመኝነት አልጠግብም ባይነቱ ገኖ በመወጣቱ ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነ።

ኢህአዴግ የማይገሰፁና የማይደፈሩ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር የከፈለውን መስዋዕትነትና እነዚህ መብቶች ምሉዕ በሆነ አኳኋን ለማስከበር መሠረታዊ ህጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተቋማዊ ማዕቀፎችን እንዴት እንደሚያያቸው አሁን አሁን ግልፅ እየሆነ የመጣ ነው።የኢህ አዴግ መንግስት ልማታዊና በዲሞክራሲያዊ አጀንዳ ስም ሰብአዊ መበቶችን በመጣስ ያለፈ ለሰው ልጆች መሰረታዊና አስፈላጊ መሟላት ሳያደርግ በፖለቲካ፣ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ቀውስ ህዝቡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎዱት በመሄድ ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት በዋናነት ጉዳይ ቢሆንም የዲሞክራሲያዊ መጣፋት፣የሰብዐዊ መብት መጣስ የሠላም መናጋት የሚያስከትለው መዘዝ ለሌሎችም መትረፉ አይቀርም።በመሆኑም ለዲሞክራሲ ስርዐት የምናካሄደው ትግል ለኢትዮጵያ በጎ አመለካከት ባላቸው የውጭ ወዳጆችና በአለም አቀፍ ማህበረሰብም ሊታውቅና ሊደገፍ ይገባል።በውጭ አገር ነዋሪዎች ዘንድ ሠላማዊ ትግሉ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ ለገዢው ፓርቲ ሠላም እንዳልፈጠረበት የታወቀ ነው።ለምሳሌ፡_ ኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን) በሚያቀርባቸው ዝግጅቶች በማህበረሰቡም ዘንድ እየተወደዱ ተቀባይነታቸውም በፍጥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ለመቀበል ትግስት ያጣው የወያኔ(ኢህአዴግ) መንግስት የሚድያ ተቋማትን፣በፖለቲካ አመራርና አባላትን ፣ፖርቲዎችንም ለማዳከም የተቀነባበረ አፈና ግፍ ፈፅሟል።ድርጅቶች መሪዎች ፣አባሎቻቸው፣ደጋፊዎችንም ጭምር በተለያዩ ወህኒ ቤቶች ታስረው ተሠቃይተዋል እየተሰቃዩም ይገኛሉ።በመላ ሀገሪቱ ከተማና ገጠር የሚገኙ የፖርቲዎች አባላት በመንግስት ታጣቂዎችና ካድሬዎች የሚፈፀምባቸው የሠብአዊ መብት ረገጣ ቃላት ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ነው።በመንግስት መገናኛ ብዝሁን በገዥው ፖርቲ ልሣኖች በተከታታይ የሚነዛው አሉባልታ የስም ማጥፋት ዘመቻም ከፍተኛ ነው።

በዚህ ዘመን አለም ስተሻለ ለውጥ በሚሯሯጥበት ዘመን ላይ የሰብዐዊ መብቶች መሠረታዊ አንዱ መብቶቻችን “ በገንዘብ የማይገዙ የማይሸጡ የማይለወጡ ከማንም የማይወረስና ለማንም የማናወርሳቸው” ባህሪያት እየለመንን የምንኖርበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባዋል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
አስተያየት አድራሻ:- tewodrosdagmawi@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: