መንግስት በጸጥታ ዙሪያ የቴፒን ህዝብ ሰበሰበ

esat
በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል።
ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩን የምትፈጥሩት እናንተ ሆናችሁ ሳለ እኛን መፍትሄ አምጡልን ማለታችሁ ተገቢ አይደለም በማለት በከተማዋ የሚታዩ የጸጥታና የኢኮኖሚ ችግሮችን በማንሳት ለባለስልጣኖቹ ሲያስረዱ ውለዋል። ሀሙስ ከሰአት በሁዋላ በቴፒ መውጫ በሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቅኝት ማድረግ መጀመራቸውና አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ መሰማቱ በከተማው ህዝብ ላይ አለመረጋጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቴፒ ካምፓስ ፈንጅ ተገኝቷል በሚል የተጠናከረ ፍተሻ ሲካሄድ ሰንብቷል።
የሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች ከፌደራልና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንደሚያደርጉም የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ ለወራት በጋምቤላ በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ። ቁጥራቸው 50 የሚጠጉ የጋምቤላ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው ዘግቧል።“ከጋምቤላ ክልል የመጡት ዜጎች በአራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ተመሳሳይ ሰዓት የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ የሚቀርቡ በመሆኑ በዚህ ችሎት ለመታደም የሄደው ህዝብ ከጋምቤላ የመጡትን ዜጎች ተከትሎ በተደረገው ጥብቅ ምክንያት ከፍተኛ ፍተሻ ” መደረጉን ገልጿል፡፡ ጥቅምት 19/ 2007 ዓ.ም ወደ ማታ አካባቢ ከጋምቤላ የመጡ በርካታ ዜጎች በአውቶቡስ ተጭነው ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡መንግስት በክልሉ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ግጭት ሲፈጥሩ ነበሩ ያላቸውን ሰዎች መያዙን አስታውቋል። የአካባቢው ግጭት የህወሃት ሰዎች ከሚያደርጉት የመሬት ቅርምት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች መግለጻቸውን ተናግረዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: