ለሕዝብ ድምፅ ጆሮ የሌለው ልማታዊ መንግስት

ናትናኤል በርሔ (ኖርዌይ)

IMG_4749የኢትዮጵያ መንግስት(EPRDF) በ1988፣1992፣1997 እና 2002 ዓም አገር አቀፍ የምርጫ እንቅስቃሴ አድርጎዋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ላለፉት 24 ዓም በሞኖፖል ያስተዳደረ መንግስት ሲሆን በዚሁ አገዛዝ ዘመን በዘር፣በጎሳ፣በሃማኖት የመከፋፈል እያስተዳድረ ሲሆን በ 2002 ዓም ላይ በተደረገው የምርጫ ዘመን በፓርላማ በነበረው 547 የምርጫ ወንበር ውስጥ 545(99.6%) በብቸኝነት ያሸነፈ መንግስት ነው። በሚመጣው ዘመን 2007 ዓም እነሱ እንደሚሉን ከሆነ የምርጫውም ውጤት 11% ያሳድጉት እና 547 መቀመጫውን ይወስዱት ይሆን ? አሁን እንኳን ስለምርጫ ለመናገር ሳይሆን በአገራችን ውስጥ እየተፈፀመ ስላለው ዜጎች ከቀያቸው (መኖሪያ ) አካባቢ ሳይፈልጉ መፈናቀል፣ መሰወር ፣ የሰራ ዋስትና ማጣት ፣ሰብዓዊ ክብራቸውን ማዋረድ፣ያለበቂ ማስረጃ ማሰር፣ እና ሌሎችንም ምክንያቶች እየተጠቀመ የሚያደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተስፋፋ በመሔድ ላይ ይገኛል። አንዳንድ ግዜ መንግስት በማን አለብኝ ያሰራቸውን ሰዎች ፍርድ በቤት ለማቅረብ መረጃዎችን አይኖራቸውም ስለዚህ ያለው አማራጭ እስረኞቹ እንዲናዘዙ ማድረግ ብቻ ነው።ለምሳሌ በኢትዮጵያ ወንጀል መቅጫ ህግ አንቀፅ 27 መሰረት አንድ ተከሳሽ ወንጀሉን ሰርቻለሁ ብሎ የእምነት ቃሉን እስከሰጠ ድረስ መረጃ ባይቀርብበትም እንኳን ተጠያቂ ይሆናል።

በ1997 እስር ቤት ውስጥ በድብደባ ህይወታቸው ካለፉ ግለሰቦች መሃከል ፣

1.ገድሉ አየለ ሁሉአንተ

2.ፀጋዮ አየለ ይግዛው
3.እርጋት(አርጋት) ጎበና ማሩ

የተባሉ ግለሰብ በደረሳባቸው ከፍተኛ ድብደባና ህክምና በመነፈጋቸው ህይወታቸው አልፎዋል።እንዲሁም ውቢት ሌንጋሞ የተባለች ነፍሰጡር ሴትም ክፉኛ በመደብደቧ ጽንሷ አጨናግፈውታል።

በቅርቡ በ2006 ዓም ዘመን ብቻ

1.ተስፋሁን ጨመዳ

2.ኒሞና ጥላሁን

3.ኑረዲን ሀሰን

4.አህመድ ነጃሺ
ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ዜጎች ለነፃነት በሚያደርጉት ትግል ዛሬም አሁንም እየሞቱ ይገኛል።

“ጠመንጃን ተገን አድርጎ በህዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓትና አራማጆቹ፤የህዝብን ሰላማዊ ኑሮ ለማተራመስ አማራጭ አድርገው እየተጠቀሙበት ያለው ስልት “ጠንካራ ናቸው

የሚሉዋቸውን” ተቃዋሚዎች ወደ ዘብጥያ መወርወር ሆኗል”
የኢሕአግ መሰረታዊ ዓላማም ወታደራዊ ሃይሉን መከታ አድርጎ በሕዝብ ጫንቃ ላይ በጉልበት የተጫነውን የወያኔ አገዛዝ በተባበረና በሁለገብ የትግል ስልት ለሕዝብ ወሳኝነት እንዲበረከክ ማድረግና ከአንድነትና ከዴሞክራሲ አንፃር ሀገሪቱ የተደራጀ ሃይል በማጣቷ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ትግሉ ያለው መራራነት ግልፅ ቢሆንም አማራጭ ለዚህም መፍትሔው በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ገዥውን መንግስት ከስልጣን ማወረድ ነው።ህዝቦችን በዘር፥ በብሄር፥ በቋንቋ፥ በሀይማኖት፥ በቀለም፥ ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት፥፥ እርስ በእርስ እንዳይስማሙ፥ አብረው እንዳይኖሩ፥ አንድንት እንዳይፈጥሩ፥ በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ፥ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ፥ ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ።

“ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት፥በመልካም አስተዳደር፥በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ፥፥ ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፥ ነፃ ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ (ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ) ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ በተጨማሪም በከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ከሀገር ውጨ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፉዋቸውን ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ማፈንና ከነዚህም ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን ግለሰቦች ኮተት የሆነ የውሸት ክሶች በመደርደር በአሸባሪነት እየከሰሰ ህዝቡ መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም አድርጎዋል” የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ነፃነት “በእርግጥ ሀሳብን በነፃነት መግለጽ አሸባሪነት ከሆነ፤”አሸባሪዎች”ተባሉትን ጋዜጠኞች ብዕር አንስተን ጥቁር ሽብር ያፋፈመውን ወያኔ ኢህአዴግን በሽብር ማንቀጥቀጣችን በእርግጠኝነት የሚቀጥል ይሆናል” ሲሉ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበርና በስደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። Article 19 ማንኛውም ሰው ነፃ ፕሬስ በነፃነት የማንሸራሸር መብት አለው ብለው ያምናሉ።በ አፍሪካ ካሉት ጨቋኝ አፋኝ ይሉት አገራት ግን ይህን የመሰለ መብት ለመተግበርም ሆነ ለመፈፀም ፈቃደኝነት ካለመታየቱም በተጨማሪ “በሽብርተኝነት ስም” እየፈፀባቸው ያለውን ግፍና በደል አገርን ጥሎ ለመሠደድ ያበቃቸውል።

በአሁኑ ጊዜ በትንሹ ከ250 በላይ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በስደት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ይህን ያህል ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች ከአገር በማሰደድ ኢትዮጵያ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር እንደሆነች፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ) በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በ2014 እአአ አሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ እስቴት ዘገባ ከሆነ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ ያላትን አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እያስቆለቆለ እና እየባሰበት በመወረድ ላይ ይገኛል።በዘገባም ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ጉዳዮችን ፌደራል ፖሊስና የፀጥታ ቡድን አባላት በተናጠል፣ በቡድን በማድረግ ግለሰቦችን ከተፈጥሮ ውጭ ህገወጥ ግርፋት፣እስራት፣መግደል ይፈፀማሉ።ያለ በቂ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስራት መዳረግ የግለሰቦችን እና የቡድን መብት መጣስ፣ጋዜጠኞች፣ብሎገሮች እንዲሁም የመጽሔት አታሚዎችን እና ባለንብረቶችን ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ መብቶችን መንፈግ።የመሰብሰብ መብት በተቃዋሚ ፖርቲዎች ላይ የስልጣን ጉልበት በሀይል በመጠቀም በፀጥታ ሀይሎች እና በፌዴራል ፖሊስ ተፅእኖ በመፍጠር በመበጥበጥ ሊገኙ ይችላሉ በሚባሉ ነገሮች ላይ አፍራሽ ሃሳቦችን በመፍጠር የመንግስት ሠላዮች አብሮ በማስገባት ብጥብጥ ሁከት መፍጠር ስራየ ብሎ ተያይዞታል።እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሁለተኛ አለም የሚኖሩ ህዝቦች ጨቋኝ መንግስት ዜጋዎቹን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር (human traffiking ) የመጀመርያ መጨረሻው ነው።

ፀረ ሽብር ህግ በመንግስት ህግ ሆኖ በወጣበት ቅርብ አመታት ጊዜያት ብዙዎችን ለእስራት፣ግድያ እንዲሁም በውል በቁጥር ለማይታወቅ ዜጋ ለስደት ዳርጎታል።እንደ ሰብዓዊ መብት ተማጋች  (human Right Watch) እምነት ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ  consisted to express their right to freedom of expression ይህም ማለት ህጉ ምን ያህል አፋኝ እንደሆነ ለመጥቀስ ይክል በትንሹ March 2011-December 2011 ብቻ በዚሁ ወራቶች 108 የፖለቲካ አባላት አመራር እንዲሁም 6 ጋዜጠኞችን ለእስራት የዳረገ አፋኝነቱን ያመለክታል።አንድ የአንጎላ ጋዜጠኛ እንዳለው ከሆነ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ በመግለፃቸው ምክንያት በገፍ ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ ህብረቱ ዝምታን መምረጡ እጅግ አሳፋሪ ነው ሲል ተናግሮዋል። አያይዞም አንጎላዊ ጋዜጠኛው ራፋየል ሲነገር ጋዜጠኞች በእስርና በእንግልት እየተሰቃዩ ባለበት ሁኔታ የህብረቱ አዲስ አበባ መቀመጥ አስመሳይነት ነው ብሎ አክሎዋል 53 አገሮችን የሚወክለው የአፍሪካ ህብረት ለሰብአዊ መብትና ለግልጽነት ቀርጠኛ መሆኑን ይግለፅ።አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚንገላቱ ለሞያ አጋሮቻቸው መቆርቆር አለባቸው።ይህ ሁሉ በደል እየተፈፀመ ባለበት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ባለቤት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች የህብረቱ መቀመጫ በሰብአዊ መብት አያያዝ መልካም ስም እና ዲሞክራሲ መብቶችን ወደ ሚከበርበት አገሮች መዘዋወር እንዳለበት ዘመቻ መጀመር አለባቸው ብሎዋል።

የ ፖለቲካ ነፃነት ስንል በፖለቲካ ለህብረተሰብ ይበጃሉ ይጠቅማሉ እንዲሁም ለአገሪቱ ካለችበት ብሔራዊ ጥቅም የተሻለ የተለወጠ የእድገት ለውጥ ለማምጣት የሚከናወንበት መድረክ ማለት ነው።በእኛ አገር ግን ይህን የመሰለ ፖለቲካን በነፃነት ለማራመድ ካልታደሉት አገሮች ተርታ ትመደባለች።የፖለቲካ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ማለት የተገላቢጦሽ በገዢው መንግስት መፈረጅ ነው።ለዚህም ምሳሌ አስረጂነት የአንድነት ዲሞክራሲና ፍትህ ፣የሰማያዊ ፖርቲ፣የግንቦት 7 አመራርና ሌሎችም አባላት ላይ እየተደረገ ያለው ነገር ለዚህ ሁሉ አስረጂ ነው።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የመብት ገፈፋ የድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ ከ357 እስር ቤቶች በላይ ይገኛል ከዚህ ውስጥ ዴዴሳ፣ጦላይ፣ታጠቅ፣ብር ሸለቆ፣ዝዋይ፣ብላቴ፣ሰንቀሌና በሌሎችም ማረምያ ቤቶች 37,000 በላይ ሰዎች የፖለቲካ እስረኞች ሆነው በየእስር ቤቶ እየተሰቃዩ ይገኛል።

የሲቪክ ማህበራት ግንኙነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዘመን ቁርኝነት ከነበራቸው መሰል ማህበራት አንዱ ነው።እነዚህ ማህበራት የበጉ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጄንሲ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 2009 እኤአ ከወጣው አዋጅ ማህበራትን የሚሰጡትን አገልግሎት በማፈንና ከአገልግሎት ውጭ ከማድረጉም በላይ የብዝሀን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት አሳጥቷል።ከዚህም አፋኝ አዋጅ የሲቪክ ተቋሞችን ሊገኝ የሚችሉን የአለም አቀፍ መብቶችን፣የሰብአዊ መብት፣የሴቶች መብት፣የህፃናት መብት፣በህገመንግስታዊ ስም የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት ለማስታረቅ ከመርዳታቸውም በላይ የሰውን መብት ለማስከበር ይረዳሉም ይጠቅማሉ።ያለመታደል ሆኖ የሲቪክ ተቋም የዚሁ አካል ተተቂም ለመሆን ቻለ።

ከቀያቸው በልማት ስም ማፈናቀል የተለመደ ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው።አንድን አካባቢ በልማት ስም ሲፈናቀሉ ዘርን(ብሔር) መከታ ያደረገ ነው። መሰረተ ልማት የሚፈለግን አካባቢ በመጀመሪያ ለህብረተሰቡ ፍላጎት መሟላት የሚገባቸው መሰረታዊ ስራዎችን መስራት ተገቢ ነው።ከክልሉ የሚነሱ የጤና፣የትምህርት ቤት፣የውሀ መጠጥ፣በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ መሆን አለበት።ማፈናቀል ማለት የህብረተሰቡን የማህበራዊ ኑሮ በማናጋት ህዝብን ወዳልተፈለገ ስደት፣ለጎዳና መዳረግ ነው።ለዚህ ሁሉ ማሳያ ይሆን በአለም አቀፍ ያለን ደረጃ እንመልከት።

-2009-2012 Global Competives index Ethiopia 118 ከ 133

-2009 Global Peace index Ethiopia 128 ከ144

-2011Corruption Perceptions index Ethiopia 120 ከ 182

-2012Human Developemet index Ethiopia 173ከ187

-2014 Global Slavery Index Ethiopia 71 ከ 167

-2014ReporterWitthoutBoarder Index Ethiopia 143 ከ 180

*ሰብአዊ መብቶቻን ለመመለስ የግድ ልማታዊ መሆን አየጠበቅብንም መብታችን ይመለስ።

*ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ በማንኛውም መልኩ የስልጣን ጥምን ማራዘም አይቻልም።

ቸር እንሰንብት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
አስተያየት ለመስጠት:- tewodrosdagmawi@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: