አንድ የአርበኞች ግንባር አባል በእስር መቀጣቱ

EPPF3
አርበኛ ጋሻው ሽባባው በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ4 ወራት ሲፋለም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊቱ የ4 አመት ከ8 ወር እስራት እንደፈረደበት ገልጿል።
አርበኞች ግንባር በወቅቱ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥቃት ከ60 ያላነሱ የመንግስት ወታደሮችን መግደሉን አስታውቆ ነበር። መንግስት ምንም አይነት ጦርነት እንዳልተደረገ ሲያስተባብል ቢቆይም ከሁለት ወር በሁዋላ በጸረ ሰላም ሃይሎች የተደረገውን ወታደራዊ ጥቃት መመከቱንና ከፍተኛ ድል ማግኘቱን ገልጿል።
መንግስት ተመሳሳይ ጥቃት ይፈጸም ይሆናል በሚል ስጋት ሰሞኑን ጦሩን ወደ ድንበር አካባቢ እያንቀሳቀሰ ይገኛል። መንግስትን በሃይል እናስወግዳለን በማለት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች መካከል አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ውህደት ለመጀመር መስማማታቸው ይታወቃል። የእነዚህ ሃይሎች መዋሃድ በአካባቢው ላይ የሚፈጥረው የጸጥታ ስጋት ያሳሰበው ብአዴን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ ህዝቡ ጸረ ሰላም ሃይሎችን በንቃት እንዲጠብቅ ተማጽኗል። በጠረፍ አካባቢ ያሉ ታጣቂዎች የጦር መሳሪያቸውን እየተቀሙ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም መረጃ ያቀብላሉ በማለት የሚጠረጥሩዋቸውን እዬያዙ በማስር ላይ ናቸው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: