ወያኔን የስልጣን ጥመኝነቱን በቃህ ልንለው ይገባል !

0040_-_Stop_Dictatorship_1_largeቴዎድሮስ ገዛኸኝ
ዛሬ በሀገራችን ያለውን የተወሳሰበ ሁለገብ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያደረሰው በመንግስት ስርአቱ አመሰራረትንና በስርአቱ ላይ ባለው እንቅስቃሴ ወሳኝ ያለው ሚና መጫወት አለመቻሉ ነው። በዚህም መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ
– ሕዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑን አምኖ አለመቀበል
– የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት አለማሟላት
– የግል ጥቅምን ከአገር አስበልጦ ማየት እና መሰሎች ናቸው።
የሰብአዊ መብቶች እና ነፃነት አለመከበር በግለሰቦች ላይ ግፍና መከራ ከማምጣቱም በላይ ግጭትና አለመረጋጋት እንዲሁም ፖለቲካዊ መስታጋብርን ይፈጥራል።ሰው በአንድ በኩል በማንኛውም ጉዳይ ላይ የመወሰን ነፃነት እንዳለው ያውቃል።ይሄ ውሳኔ ጠንከር ያለ መዘዝ ባላቸው ጉዳዮች ላይ የሚሰጥ ከሆነ ደግሞ የበለጠ ያወሳስበዋል።

የነፃነት ፍራቻ ብዙዎቻችን ህሊናችን የማይቀበለውን ድርጊት እንዲኖረን የሚያደርገን ዋናው ምክንያት ነው።የውሳኔያችን መዘዝ ለመቀበል ድፍረቱን ስናጣ በሰውነታችን የተላበስነውን ሁኔታዎችን የመቀየርና እምቢ የማለት የነፃነት ያለን ፍጥረት መሆናችንን መካድ የተለመደ ነው።ያለንበትን ሁኔታ ለመቀየር ምርጫ የሌለን አድርገን እራሳችንን ማየት እንጀምራለን።ለራሳችን እየዋሸን ምንም አይነት የሰብአዊነት ሞራል የሌለው ኑሮ እንኖራለን።
የተፈጥሮ ሰብአዊ ነፃነታችን ላይ የሚደረገው ትግል ቀላል አይደለም።ይህንን ትግል ለመመከት በሚገባ ካልተዘጋጀን በራሳችን ምርጫ ይሁን ወይም በሌሎች ውሳኔ ከነፃነት ወደ ባርነት የምናደርገውን ሽግግር የሚያስቆመው አይኖርም።
የነፃነትን ጉዳይ ፍርፋሪ እየለቀመ በውርደት የወያኔ ጌቶቹን አይንና ጆሮ ፈርቶ የሚኖረው ሆድ አደረሩ ያውቀዋል።ለጥቅማ ጥቅም ብለህ ስራ ለመቀጠር፣የደረጃ እድገት፣እርዳታ፣ለማዳበርያ፣ለምክር አገልግሎት ለማግኘት፣ለትምህርት ዕድል ወይም ለሌላ ማናቸውም ጥቅም አሊያም ከዘወትር አገልግሎት ለማግኘት የወያኔ ጀሌ የግድ መሆን የለብህም።አንድ ዜጋ በዘሩ እየተለየ ጥቃት ሲደርስበት፣በእምነቱ የተነሳ ሲዋረድ፣እየተገፈፈ ያለው ከሰብእናውን ጋር የመጣውን ነፃነቱን ነው።
ኢትዮጵያን የሚመሩ መሪዎች በየጊዜው የመጡ አምባገነን መሪዎች እንደ ቆሻሻ እየጠረጉ አያት ቅድመ አያቶቻችን በየሜዳው በየዱሩና በየጫካው እየወደቁ ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነቱን አስረክበውናል።እኛም ብንሆን ይህችን ሀገር ሲቻል ከቀደምቶቻችን በተሻለ ካልሆነም እንደነበር ለመጪው ትውልድ ከማስረከብ የላቀ የትውልድና የታሪክ አደራ እንዳለብን እናውቃለን።ስለ ሀገራችን ስናስብ የማናመልጠው እውነታ ቢኖር እኛ መርጠን የተወለድንበት ቦታ አለመኖሩ ነው።ወላጆቻችን አልመረጥንም፣የተወለድንበትን የቤተሰብ አይነት አልመረጥንም፣ቋንቃችንን አልመረጥንም፣የቆዳችንን ቀልም አልመጥንም። ለብዙዎቻችን በአረንጋዴው፣ቢጫው በቀዩ ስም ኢትዮጵያዊነት የምንረው ይህ ነው።

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብእና መራከስ ውርደትና አሰቃቂ ድህነት እያየን እንዳላየን ማለፍ የምንችለው ቀደም ብለን እራሳችንን ከሰውነት አውርደን በእኔ ላይ ካልደረሰ ምን አገባኝነት የመጣ ነው።መንግስት ከማናቸውም ማህበራዊ ተቋማት በተለያየ በአንድ ጂኦግራፊያዊ ክልል ውስጥ ያሉ ህዝቦችን ያስተዳድራል በግል ሊሰራ የማይችሉ ግን ለማህበረሰቡ የሚያስፈልጉ ግልጋሎቶችን ይሰጣል የማህበረሰቡን ደህንነት ይጠብቃል።መንግስት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን መገላገልና መዳኘት….. ወዘተ የመሳሰሉ መሰረታዊ ስራዎችን የሚሰራ ተቋም ነው።ይህን በሞኖፖል ሀይል የሚጠቀምበት አግባብ፣ የዚህ ተቋም አፈጣጠርና አቋቋም፣የተቋሙ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው አጠቃላይ ግንኙነት፣የተቋሙ ስልጣን መጠን፣የስልጣኑ ምንጭ…….ወዘተ በአጠቃላይ የዚያን የፖለቲካ ማህበረሰብ አይነት ወይንም ማህበረሰቡ የሚተዳደርበትን የፖለቲካ ስርአት ምንነት ይወስናል። ስልጣን የህዝብ ነው ስንል መንግስት የሚኖረው ሆነ የሚንቀሳቀስው ህዝብ በከፈለው ግብርና ቀረጥ እንዲሁም በሕዝቡ ስም የሚበደረው ገንዘብ ነው።

ወያኔ በሀገራችን ላይ እየፈፀመ የሚገኘውን ስውር የቅጥረኝነት ተግባሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በተለያዩ የዜና አውታሮች እየተገለጸ ይገኛል።ሊደብቀውና ሊያመልጥበት ያልቻለው ስውር ምግባር ሕዝብን በርሀብ አለንጋ እየተጫወተ ያለው ሚና ምን ያህል ለሀገርና ለወገን ደንታ ቢስነቱን ያሳያል።በቀደሙት አመታት የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ “በቅኝ ግዛት ያሉ የአፍሪካ ሀገሮች ነፃነታቸውን እስካላገኙ ድረስ፣ኢትዮጵያ ራሷን እንደ ነፃ ሃገር አትቆጥርም ይል ነበር።” ይህንንም የፖሊሲ ውሳኔ በተግባር ለመተርጎም የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች።ለአፍሪካ አገራት አቅሟ የፈቀደላትን ዕርዳታ ሁሉ በቅኝ ገዢዎች ስር ያሉ የደቡብ አፍሪካን የነፃነት ታጋዮችን እነ ኔልሰን ማንደላን ጭምር አሰልጣና ከቅኝ ገዢዎቻ ነፃነትን አስገኝታለች አንደ አሁኑ “ፖሊሲ ገረድ” ተብሎ በፖሊሲ ከመረቀቁ በፊት ኢትዮጵያዊነት የማለት ስሜት በራሱ ከነፃነት ጋር የተሳሰረ ነው። እኛም ጠንክረን ወያኔን አስወግደነው ሀገራችንን ከጥፋት አደጋ መላው ሕዝባችን መታደግ ግዴታችንን መወጣት አለብን።ማን ለሀገሩና ለሕዝቡ ጥቅም እንደቆመ ለይቶ ማወቅና ሀገርን ለመጠበቅ ነቅቶ ማታገል ነው።ወያኔ ዛሬ ሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሁሉ ማለትም ከጉሊት የችርቻሮ ንግድ ሽያጭ አንስቶ እስከ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ይለው ንግድ ሁሉ በወያኔ ቁጥጥር ስር ነው። ትራንስፖርት ፣ ሆስፒታሎች፣ባንኮች፣ኢንሹራኖች፣የግል ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች፣የከተማ ቦታና የገጠር መሬት ሁሉ ወያኔ እንዳሻው የሚያዝባቸው የግል ንብረቶቹ ናቸው።
በርካታ በውጭ የምንኖር ገንዘባችንን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለሚጨፈጭፉ፣ለሚያስሩ፣ለሚያሰድዱ፣በረሀብ ለሚፈጁ፣በበሽታ ለሚሰቃይና ግዛታችን ለባእድ ሀገሮች ለሚሰጥ ወንጀለኛ መንግስት በገፀ በረከትነት የምንሰጠው በምን ምክንያት ነው ? የሚፈፀምብን ግፍና በደል በፍጹም አልሰማም ብሎናል፣የወያኔ ባርነት እንደ ማር ጥሞናል።በረሀብ፣በድህነት፣በስራ አጥነት፣በተለያዩ በሽታዎች ለሚያልቀው ሕዝባኝን ከማዘን ይልቅ ለወያኔ ማሰብና መጨነቅ ይቀናናል ግዜ እንስጣቸው። የዲሞክራሲ ግንባታ ቀስ በቀስ ነው፣ የሚሉት አባባሎች ጆሮአችንን ያሰለቹን ናቸው።ዜጎቻቻን የሚምቱት ከኪሳችን እያወጣን በምንሰጣቸው አንጡራ ገንዘባችን መሆኑን የለበትም። ስለዚህ ካሁን በሗላ ወያኔን የስልጣን ጥመኝነቱን በቃህ ልንለው ይገባል።አንድነት ኃይል ነው !!
ድል ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: