በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ መሀልየተደረገውን ውህደት በተመለከተ የተሰጠ የድጋፍመግለጫ፣

630x343xDCESON-Logo-630x343.jpg.pagespeed.ic.5EB12q_HGRአምባገነኑ የወያኔ መንግስት በሀገራችን ታሪክ በሥልጣን ላይ ከመጡ የገዥ ሃይሎች ጋር ሲወዳደር ሀገርን ለከፍተኛ አደጋ በማጋለጥ፣ ሕዝቧን በማወረድ፣ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ዕኩይ ሃይል መሆኑ ከማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም። ድርጅታችን ይህንን በአገራችንና በህዝባችን ላይ የወደቀውን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ አገራዊ አንድነቷ የተጠበቀ የህዝቧ እኩልነትና የህዝብ የበላይነት የተረጋገጠባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚደረገው ትግል ለተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ድጋፉን በመስጠትና የሚጠበቅበትን የዜግነት ግዴታ ለመወጣት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7 ለፍትህ፤ዴሞክራሲና የነጻነት ንቅናቄ በተናጥል የሚደረገውን ትግል በመተው ለኢትዮጵያ ዜጎች መብት እኩልነትና ነጻነት መከበር ተዋህደው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በሚባል መጠሪያ ለመታገል ጥር 2/ 2007 መወሰናቸውን ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ በደስታ የተቀበለው መሆኑን ይገልጻል።ድርጅታችን የአገርና የህዝብ ጠላት የሆነውን ህውአት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ግፍና በደል ለመታደግ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሚያደርገው ቁርጠኛ ትግል አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለመስጠት ቃል ይገባል።

እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችም ከድርጅቶቻቸው ጠባብ ፍላጎትና ስሜት በመላቀቅና የሀገርንና የህዝብን ጉዳይ በማስቀደም በጋራ በመሰባሰብና በመታገል የወያኔን ግብአተ መሬት እንዲያፋጥኑ ጥሪአችንን እናቀርባለን።

አንድነት ሀይል ነው!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: