ውስጥ አዋቂ ፕሮግራም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

10750215_481813495291444_8118182720849295080_o“ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሚዲያዎችን የማሸማቀቅ ስራ ነው የሰራው”
አቶ ብርሃኔ ንጉሴ

በዛሚ ዘጠና ነጥብ ሰባት ኤፍ ኤም ሬዲዮ በኢትዮፒካ ሊንክ አማካኝነት የሚተላለፈው የውስጥ አዋቂ ፕሮግራም በብሮድካስት ባለስልጣን የመጨረሻ ማስጠንቂያ የተሰጠው ሲሆን ይሄንንም ውሳኔ ዛሚ 90 ነጥብ 7 ሬዲዮ ጣቢያ እንዲያስፈፅም ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ልኡል ገብሩ ማክሰኞ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ብሮድካስት ባለስልጣን በሰጠው በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፤በባለስልጣኑ ቦርድ በኩል በተሰጠው ውሳኔ መሰረት በዛሚ 90 ነጥብ 7 ሬዲዮ ጣቢያ ላይ የተሰጠው የእግድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በጣቢያው ከሚተላለፈው የኢትዮፒካሊንክ ፕሮግራም ውስጥ አዋቂ ፕሮግራም በፈፀመው ጥፋት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው የተወሰነ መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል። ኃላፊው በዚሁ መግለጫቸው ውሳኔው የአመልካቾችን መልስ የመስጠት መብት በተመጣጣኝና በተመሳሳይ ሰአት በማስተላለፍ ቅሬታቸውን እንዲገልፁ የሚያደርግ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው አመልክተዋል።
በዚሁ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡን የአክሱም ፒክቸርስና የኢትዮፒካ ሊንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና አዘጋጅ አቶ ብርሃኔ ንጉሴ ብሮድካስት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያዘኑ መሆኑን አመልክተዋል። “ጉዳዩ በዚህ ደረጃ አድጎ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎችን ጠርቶ መግለጫ እስከመስጠት መድረስ የማይገባው ነበር” ያሉት አቶ ብርሃኔ፤ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የሰጠው መግለጫ የዛሚ 90 ነጥብ ሰባትና የኢትዮፒካ ሊንክ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሚዲያውን የማሸማቀቅ ስራ ነው፤ ብለውታል። ባለው የህግ አግባብ መሰረት በሚዲያዎች በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ቅሬታ ያለው ማንኛውም አካል ለብሮድካስት ባለሥልጣን ሲያመለክት ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሁለቱንም አካላት አወያይቶ የተላለፈው ፕሮግራም ፍትሃዊ አለመሆኑን ካረጋገጠ ተበደልኩ ያለው ሰው በዚያው ፕሮግራም እድል ተሰጥቶት ሃሳቡን እንዲገልፅ የሚደረግ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ብርሀኔ፤ የተበደልኩ ጥያቄ ላቀረቡት አቶ ዳንኤል ተገኝ እድሉ ቢሰጣቸውም ያልተጠቀሙበት መሆኑን አመልክተዋል።
ሆኖም ባለሥልጣኑ ይሄንን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ውሳኔና መግለጫ የሰጠ መሆኑን የገለፀት አቶ ብርሀኔ በውሳኔው ከጀርባው ሌላ ነገር አለ የሚል ጥርጣሬ ያላቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። እሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከዚህ ቀደም በሰሯቸው ፕሮግራሞች ምንም አይነት የክስ ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን በመግለፅ የብሮድካስት ባለስልጣንም ከውሳኔው በፊት ይሄንን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ የነበረበት መሆኑን አመልክተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: