እውነተኛ ፍላጎታችን ኢትዮጵያን መታደግ ከሆነ ለኢትዮጵያ ስንል ሁሉን እናድርግ

12025586_739718782801011_703816740_nቴዎድሮስ ገዛኸኝ

ስለ ታላቅዋ የአፍሪቃ እንቆቅልሽ፤ ስለ ሥልጣን አያያዝና ሥልጣን ላይ መውጣት፣ ሥልጣንም ላይ መሰንበትና ከእሱም አልወርድም ማለት ምን እንደሆነ እንድናስብ እንድናውቀው ተጨባጩ ሁኔታ እንደሚያሳየው ለአንድ አምባገነን ለዚያም አስተሳሰብ ልቡን ለሸጠ ሰው ይህ ሆድ አደር ትልቅ ቦታ አለው። ያለመታደል ሆኖ ሗላቀር የሆኑ አገሮች በተለይ በአፍሪካ በመሪነትና በወሳኝነት ቦታዎች ላይ የሚቀመጡበት አብዛኞች በልምድና በስነምግባር የተራቆቱ ስለሚበዙባቸው በራሳቸው ስለማይተማመኑ ገንዘብ ማጋበስና በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ውሸትና ማታለል ይበዛሉ። ዛሬን እንጂ ነገንና ለነገው ትውልድ ደንታ ስለሌላቸው ከወገንና ከሀገራቸው ሕዝብ ይልቅ ከውጭ መንግስት ፍላጎት ጋር ግንባር ቀደም ትብብር ያደርጋሉ ከመላው አለማት በአምባገነት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው አገራት መሀከል ግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የወያኔ አገዛዝ አንዱ ነው። ላለፉት 24 ዓመታት እየተጨቆነች እና እየተረገጠች ላለችው አገሬ ኢትዮጵያ እኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔ ከሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ አንስቶ በእያንዳንዷ ዓመት የተባበረ እንቅስቃሴ የምናደርግበትን መተማመንና መከባበርን በወያኔ ጋሻ ጃግሬዎች እርዳታ የብሔር ፖለቲካ ከፋፍለህ ግዛ እነሆ ዛሬ ወያኔ ባዘጋጀልን ወጥመድ ወድቀን በመንፈራገጥ ላይ እንገኛለን። ኢትዮጵያ ብዙ ውስብስብ ችግሮች ያለባት አገር ናት። በተለያዪ ጊዜዎች እነዚህ ለራሳቸው የግል የቡድን ፍላጎት መጠቀሚያ ለማድረግ የፈለጉ ወይም እነዚህን ችግሮች ዲምክራሲያዊ ባልሆነ መንገዶች በህዝብ ስም እንፈታለን ብለው የተነሱ አምባገነን ሀይሎች የሀገራችንን ችግሮች የበለጠ አወሳስበው በመጨረሻ እራሳቸውም አይወድቁ አወዳደቅ ሲወድቁ አይተናል ይሄውም በቅርብ ጊዜ በሰሜን አፍሪካ ሆነው ማንሳት በቂ ነው። ሕወሃት ስልጣን ከጨበጠ ከጅምሩ በኢትዮጵያ የዘረጋዉ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይ ፖለቲካ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰብ አገር ናት። በታሪኳ የተሰሩ ብዙ ስህተቶችና በደሎች አሉ። በአንጻሩም ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከተለያዩ ቋንቋዎችና ክልሎች በሰላም በፍቅር ኖረዋል፣ ተዋደዋል፣ ተደባልቀዋል። በጋራ የዉጭ ወራሪ ኅይላትን መክተዋል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ከደደቢት በረሃ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቶ በመንገሥ በአባቶቻችን መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን ድንበራችን በማፍረስ፣ ከቤቶቻችን በማፈናቀል፣ መሬታችንን ለባዕድ በመስጠት ያደረሰብን በደል ጣሊያን ከአውሮፓ በመምጣት ከተቃጣብን ወረራ ካደረሰብን ጉዳት በልጦ ይገኛል። በሽፋን ስሙ ኢሕአዴግ ተብዮው ወያኔ/ሕወሐት ዕድሜውን ለማራዘም ይመቸው ዘንድ በውስጣችን ቅራኔን በማስፋት በዘር እያደራጀ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ሕዝብን በእሥራት፥ በግድያ፥ በበሽታ፣ በረሐብ እየፈጀና እያስፈጀ ፋሽስታዊ ሥርዓቱን ከጫነብን ላለፉት ሁለት አስር አመታት በላይ አልፎናል። የተቃዋሚው ጎራም ባልረቡ ልዩነቶች እርስ በርስ ባለመግባባትና ተለጣፊውም በዝቶ ትግላችን ግብና ዓላማውን ከመሳቱም አልፎ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስፈራርቶና አሽብሮ ለመግዛት በሚያደርገው ትግል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ድጋፍ እያበረከትን ነው። ከወያኔ ጋር መደራደር በሀገራችን የዴሞክራሲን ሥርዓት መመሥረት አያስችልም። ወያኔ በታሪኩ ሁኔታዎች ወጠር ሲያደርጉት ለማዘናጋት እንደራደር ቢልም በመጨረሻ ቅራኔዎችን የሚፈታው በኃይል ብቻ ነው። ከወያኔ መደራደር የሕዝቡን ትግል እጅ ለማሰጠት ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዴሞክራሲያዊ ትግል መሳካት ዋነኛው መሠረት የኃይል ሚዛንን ወደ ሕዝብ ወገን እንዲያጋድል የሚያደርግ ሕዝባዊ ጉልበት በጥንቃቄና በቁርጠኝነት ሲገነባ ብቻ ነው። ከዚያ ባነሰ አቅም መደራደር ሽንፈትን ለማረጋገጥ ነው። በጎንደር በኩል ያለ የኢትዮጵያ ሰፊ ለም መሬት ከህዝብ ደብቆ ለሱዳን መንግስት በገጸ በረከትነት በማቅረብ የውሃውን ጥልቀት ሞክሮ ዛሬ ደግሞ በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ኢትዮጵያውያንን ከሀገራቸው መሬት በሃይል እያፈናቀለ የቤልጀየምን የቆዳ ስፋት ያክል መሬት እየቆረሰ ለተለያዩ ሀገሮች ሀገራችንን እየሸነሸነ በመሸጥ ላይ ያለ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚሰራ ቡድን ነው። ይህ የኢትዮጵያ የሆነን ነገር ሁሉ ብዙ መስዋዐትነት የከፈሉት አርበኞች አባቶቻችን የሚሸጥና የሚለውጥ አፋኝ ወሮበላ መንግስት ኢትዮጵያዊነትን ሸርሽሮ በጎሳ የተከፋፈለ ደካማ ህዝብና ደካማ ሀገር ለማድረግ ይዞ የተነሳውን ዓላማ ሲሰራበት ቆይቶዋል። ይህ አፋኝ የኢትዮጵያ ጠላት የህዝቡን የሰውነት መብቱን ገፎ ከመኖር በታች ከሞት በላይ አድርጎት በረሃብ ከሚታመሰው ህዝብ ጉሮሮ እየነጠቀ ከመሬት ሽያጭ የሚያገኘውን ገንዘብ በተለያዩ የውጭ ባንኮች የሚያሸሸውንና የሚያጉረው አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ የአምስት አመት ሁለተኛው እቅድና ትራንስፎርሜሽን በሙሉ የሚነደፈውና የሚጠነጠነው ከሀገሪቱ ጥቅም አኳያ እንጅ ከእውነትና ከሀሰት ከሰብአዊነትና ከዴሞክራሲ ጋር በተዛመደ መልክ ስላልሆነ የምታወሩት ሌላ የምታደርጉት ሌላ ብለን ብናሳጣቸው ብንወቅሳቸው ለኛ ጠብ የሚል ነገር አይኖርም ። ይህ እንዲሆን ከተፈለገ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ራዕይ አንግበው ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት
ለማድረግ ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ በማንኛውም ዓይነት መልኩ በማንም ግፊት ሳይደራደሩ በጽናት የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚያታግሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ከፍተኛ አክብሮትና ድጋፍን ከመስጠት ወደ ኋላ
ማለት የለብንም። የተያያዝነው ትግል የዴሞክራሲ ብቻ ሳይሆን ሀገር አድንም መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። እንዴት ከዚህ ልንደርስ ቻልን ብለን እያንዳንዳችን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ራሳችንን ብንጠይቅና ጊዜ ሳንፈጅ መተማመንና መከባበርን እንዳ ሀገሬ ወጌሻ ለቃቅምን ከቦታው እንዲገባ መጠገን መጀመር ይኖርብናል። ይህ ጥረት ደግሞ እያንዳዳችን ትከሻ ላይ ወድቋል። ይኄው የአሜሪካ መንግስት ነው በአንድ በኩል ሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ እያለ ሲለፍፍ በሌላ ወገን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ መከራና የሰብዓዊ መብት ረገጣ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን እንደ ሰሜን ኮርያው አይነት በዓለም በዕኩይነቱ አቻ የሌለው አምባገነን መሪ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲደግፈው የሚታየው ለጥቅም እንጂ ሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ ወይም የሰው ልጅ ጣዕርና ዕልቂት ምኑም ያልሆነው የአሜሪካ መንግስትና የዚሁ ፖሊሲ አራማጅ መሪዎቹ የሶርያው ፣ የአፍጋኒስታኑ ፣ የሩዋንዳ የእርስ በርስ ፍጅት ዳር ሆነው ሲያዩ ዓለም ታዝቧል። ኢትዮጵያ፡ እንደሀገር፡ እንድትቀጥልና፡ የኢትዮጵያ፡ ህዝብም፡ ከተጫነበት፡ የመከራ ቀንበር፡ እንዲገላገል፡ ከልብ፡ የምንናፍቅ፡ ከሆነ ምኞት፡ የሚጭበጠው፡ በሥራ ነውና፡ ያለምንም፡ ማቅማማት፡ እያንዳንዳችን፡ የዜግነት ድርሻችንን፡ የምናበረክትበት፡ ቀን ቢኖር፡ ዛሬ ሥአቱም፡ አሁን፡ ነው፡ በካሀዲው፡ ጎራ ከተሰለፉትና፡ በመሀል፡ ከሰፈሩት፡ ጥቂት፡ ሰዎች፡ ውጭ ሁሉም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ማለት፡ ይቻላል፡ የወያኔን፡ ሀገር፡ አጥፊነት ከነዚህ ወጥመዶችና የተንኮል ተግባራቱ መካከል አንዱ ሰላዮቹን ለተቃዋሚዎች እጃቸውን እንደሰጡ በማስመሰል የሚታወቁ መረጃዎችን በመድገም ወይም አሳሳች መረጃ በመስጠት ባለስልጣን ነበርኩ፤ ብዙ ነገር አውቃለሁ በማለት አልፎ ተርፎም የኢትዮጵያውያን ትግል ለማዳከም አንድነትን ወገን ለመከፋፈልና የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የሚጠቀሙበት ስልት ነዉ። እኛም ሁለት አማራጭ ነዉ ያለን ከዚህ በፊት ከሰራናቸዉ ስህተቶች ተምረን ልዩነቶቻችን አቻችለን የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በኛ ላይ የሚዘረጉትን ወጥመዶች ሰባብረን፣ ይህ ችቦ የበለጠ እንዲቀጣጠል ማድረግ አንደኛዉ አምራጫችን ነዉ። ሁለተኛዉና ሌላዉ አማራጭ የሕወሃት መንግስትን እድሜ የሚያራዝም፣ የተለኮሰዉን ችቦ የሚያዳፍን፣ አገራችን ኢትዮጵያውም ከድጥ ወደ ማጡ እንድትሄድ የሚያደርግ የርስ በርስ የመከፋፈልና አብሮ ያለመሥራት አጉል ኀላ ቀር ልማዳን መቀጠል ነዉ። አንድ ግን ለማሳረጊያ ማንሳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር፣ እኛ ተከባብረንና ተፋቅረን አብረን በሰላም ለመኖር ከአወቅንበት እንደሚባለው እንደ አውሮፓውያኖች ገና ብዙ አመታት መጠበቅ ሳይሆን ነገ ማድረግ የምንችለው ነገር ነው። ያገኘነው ልምምድ የቀመስናቸው መከራዎች በቂ ትምህርቶች ናቸው። ነጻነትና ነጻ አስተሳሰብ ማለት ደግሞ ማንኛውንም ዓይነት “ባርነትን” አልፈልግም ማለት ነው።

ቸር እንሰንብት።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አገራችንን ይጠብቅልን፡፡

ናትናኤል በርሔ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: