ለተከሰተው ረሀብ የሚደርስላቸው ተጠያቂውስ ማነው?

img_3839ቴዎድሮስ ገዛኸኝ

ዛሬም እንደገና የአገራችን ስም በድርቅና በረሃብ ምክንያት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መነጋገርያ ርዕስ ሆኖል፡፡ በዝናብ እጥረት ምክንያት በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የተከሰተው ድርቅና ረሃቡ  ዓለምን እያነጋገረ ቢሆንም  የድርቅ ውጤት የሆነውን ረሃብ አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ ዜጎችን ከሞትና ከስደት ከመከላከል አኳያ የኢህአዴግ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ከዓለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያን የሚመታው ድርቅና የምግብ እጥረት ችግር በየአስር አመታት ዑደት የመደጋገም ባሕርያት ይታይበታል።የነዚህ አስር አማታት ዑደት አገሪቱን ሲመታ የቆየው ረሀብ አንድና ተመሳሳይ መነሻ ያለው ነው። ይህም የአየር ንብረት መዛባት በአንዳንድ ቦታዎች ያስከተለው የዝናብ እጥረት ነው። ዘንድሮም ከ15 ሚልዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሕዝብ ለረሀብ መጋለጣቸውን የተለያዮ የአለም አቀፍ ሚድያዎች ዘግበውታል። የዚህም የምግብ እጥረት መነሻው ኤልኖ እና ሰኔ ላይ መጣል የነበረበት የዝናብ እጥረት ይስከተለው ችግር ነው።

ዘንድሮ በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሀብ አስመለክቶ የረድኤት ድርጅቶች እና ሌሎች አገሪቱ የገጠማትን ችግር እናውቃለን የሚሉ ግለሰቦች የተለያየ አስተያየት ሰጥተዋል።የረድኤት ድርጅቶች የዘንድሮ ረሐብ የተረጂዎች ቁጥር መንግስት በይፋ እንደገለጸው 8.2 ሚልዮን ሳይሆን ከዚያ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ነግረውናል። የችግሩንም ስፋትም በተመለከት፣ የምግብ እጥረት ችግሩ እርዳታን በወቅቱ ከቀረበ በተረጂዎች ላይ ሞትና መፈናቀል ሣያስከትል በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል በለው ያምናሉ። በሌላ በኩል የረድኤት ድርጅቶች መንግስት አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ሲያደርግላቸው አይሰተዋልም።

ባለፉት ዓመታት  አርብቶ አደር ህዝብ በሚበዛባቸው ክልሎች  የሚታየው የፖለቲካና የስልጣን ሹኩቻ መቋጫ አጥቶ በመቆየቱ ምክንያት የተረጋጋ አስተዳደራዊ ስራን በመስራት መንግስታዊ ተቋማቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንዳልተቻለ ያታወቃል፡፡ ሹማምንቶቹ በስልጣን ሽሚያና ፖለቲካዊ ሽኩቻ ተጠምደው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ባለመቻላቸው ምክንያት ለህዝብ ተጠሪና ተጠያቂ የሆነ የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት አልተቻለም፡፡ በተከሰተው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ አለመረጋጋትና ክፍተት ምክንያት የህዝቡን መሰረታዊ ችግሮች የሚቀርፍና ዘለቄታ ያለው ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የልማት ስራ ካለመሰራቱም በላይ አርብቶ አደሩ የተረጋጋና የሰከነ  ህይወት ሊመራ ባለመቻሉ ምክንያት በተለያየ ጊዜ ለተደጋጋሚ ድርቅ ተጋላጭ ሆኖል፡፡

ከረሀብና ከምግብ እጥረት ተላቀው የተሻለ ህይወት እንዳይመሩ እንቅፋቶች ኢህአዴግ የሚከተላቸው የተለያዩ ፖሊሲዎች አንዱ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ ገበሬው አቅም ኖሮት ወደ ግብርና ለመግባት የሚፈልገውን ኢትዮጵያዊ ገበሬዎች መሬት በቀላሉ እንዳያገኝ አድርጓል፤ ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ያሰፈነው የዘር ፖለቲካም ዜጎች ወደ ተለያዩ ክልሎች ተዘዋውረው እንዳያመርቱ እንቅፋት ሆኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት የመንግስት ዓይነተኛ ትኩረት መሆን የሚገባው በረሀቡ ምክንያት ህይወቱ የሚያልፈው ዜጋ ቁጥር ላይ እሰጣ አገባ መፍጠር ሳይሆን አንድም ዜጋ ቢሆን እንዳይሞት የሚደረገውን ጥረት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በቂ እርዳታ ተገኝቶ  አደጋው ሳይባባስ የዜጎችን ሕይወት መታደግ ነው፡፡  እንሰሳት እያለቁ ሰው ተርቦ እየሞተ ባለበት ሁኔታ የተረጂን ቁጥር ለመቀናነስ የሚደረገው የፕሮፓጋንዳ ጥረት የሰው ህይወት ከተረፈ በኋላ ሊደረስበት ስለሚችል ቅድሚያ ትኩረት የዜጎች ህይወት በማዳን ላይ እንዲሆን፡፡

እውነታው ግን ዛሬም ኢትዮጵያ ልጆቿን ረሀብ እያለቀሰች ተቀብራለች:: ማነው የሚደርስላቸው ተጠያቂውስ ማነው?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: