ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ቢልም ተቃውሞ ግን ቀጥሎአል

12009571_452177654969272_2992392158665003976_n የኢህአዴግ አንድ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መተውን ባስታወቀ ማግስት በአምቦ፣ በአርሶ ኬፈሌና በሌሎችም የኦሮምያ ክፍሎች ተቃውሞው ቀጥሎአል።
በአምቦ የተካሄደው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ሰው መገደሉና በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። ከቆሰሉት መካከል ህጻናትም ይገኙበታል።
ከአምቦ ከተማ በተጨማሪ በ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሓ ከተማ ፣ በበደኖ፣ አርሲ፣ ሆድሮ ጉድሩና ሌሎችም ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
በሌላ በኩል ኦህዴድ ያወጣውን መግለጫ የኦፌኮው ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና አጣጥለውታል። ኦህዴድ ክልሉን የመምራት የሞራል ብቃት ስለሌለው ስልጣኑን ለህዝብ ያስረክብ ብለዋል።
ዶ/ር መረራ ፣ ዋናው ጥያቄ ” አዲስ አበባ ለምን ሰፋ አልሰፋ ሳይሆን፣ ለወደፊቱ አርሶደአሩ እንዳይፈናቀል ምን ዋስትና አለው” የሚለውን መመለሱ ላይ በመሆኑ፣ መግለጫው ይህንን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ይላሉ
በኦህዴድ የተሰጠው መግለጫ ተቃውሞውን ያስቆመዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር መረራ አይመስለኝም የሚል መልስ ሰጥተዋል። “ህዝቡ ይህ ድርጅት ወይም ያ ድርጅት ስለመራው ሳይሆን በራሱ ጊዜ ነው የተነሳው የሚሉት ዶ/ር መረራ፣ ጥያቄው ከመልካም አስተዳደር ችግር ጋር የተያያዘ መሆኑን፣ ዛሬ እንኳን ቢበርድ ነገ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: