ሁላችንም ለለውጥ እንነሳ

አገራች ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ ጊዜ ለውጥ ልትወስድባቸው የሚገባት ጉዳዮች

አሉ።ትውልዱ የለውጥ ስሜትን ሊያመጣ የሚገባበት ዘመን ላይ ነን።ለውጥTheodros Ghezahegn

ሲባል ከምን ከምን ልንል እንችላለን።አንደኛው ከጎሰኝነት እስራት፣ ከጥላቻ ፖለቲካ፣

 

ከድህነት፣  ከአምባገነኖች ጭቆና፣ ከአደገኛ ባህሎች ሁሉ ነው  አገራችን ኢትዮጵያ

ከገባችበት ዙሪያ መለስ ችግሮች ለመውጣትና የተሻለ ዓለም ለማየት ፖለቲካዊ ለውጥ

ብቻውን አይበቃትም። ሕወሓት ኢሕአዴግ ወደሥልጣን ከመጣ በኋላ የገባንበት ስስታም ፖለቲካ ደግሞ አንዱ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ክተት ልናውጅበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ አገራችን ከእኔ እኔ እኔ ከሚል ራስ ወዳድና ጠባብ አስተሳሰብ ወጥታ ወደ እኛ አስተሳሰብ መግባት ያስፈልጋታል።  የግድ ከዚህ የወጡና ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ቡድኖችን ይጠይቃል።ይሁን እንጂ ሕወሓት/ኢሕአዴግ በሻዕቢያ እየታገዘ የደርግን የአፈና አገዛዝ ማስወገዱ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት፣ ከዚያም አልፎ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊያመጣ እንደማይችል ደግሞ በወቅቱ በተለይ በአንድነቱ ጎራ አካባቢ በሰፊው ይነገር ነበር።እንደተባለውም የሕወሓት ጠባብ ብሔርተኛና ዘረኛ ቡድን ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በተለይ አንድን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ መጠነ ሰፊ የሆነ በደል ሲፈጽም ነው የኖረው።ብዙዎች ይህንን ዘረኛና አጥፊ አካሔድ ተቃውመው ሲደራጁ  በረቀቀ ዘዴ ዋና የፖለቲካ አንቀሳቃሶችን በመደለል፣ በማስፈራራት ከትግሉ ሜዳ እንዱርቁ እምቢ ያሉትን ደግሞ በየማሰቃያ ቤቱ እጅግ አሰቃቂና ዘረኛ በሆነ ሁኔታ ዘግናኝ በደል የሚፈጸምባቸው፣ ያልተነገረላቸውና ስማቸው የማይታወቅ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሉ።ለእነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መጮህ መቻል አለብን።ከዚህም አልፈን ይህ ግፈኛ ሥርዓት ከዚህ የጥፋት አካሔዱ እጁን እንዲሰበስብ ትግል ከማድረግ ውጭ ምርጫ የለንም።
አገዛዙና የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን አበክረው የሚያወሩት ባለፉት ዓመታት ስለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት ነው። ይሁን እንጂ፣ አገራችን ምን ያህል ትልቅ የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብ የፖለቲካው ሁኔታ እንደሚታየው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዘጋ ከሄደ፤  ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎች ሁሉ በጠላትነት ተፈርጀው በጥይት ሲደበደቡ እየታዘብን ነው። ድርጅቱ ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ ራሱን ወደ ሲቪል ድርጅትነት አለመለወጡ እጅግ የሚያሳስብ ብቻ  እንደሚታየው መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎች በጥይት እየተደበደቡ የሚቀጥሉ ከሆነ፤ እንደሚታየው አገዛዙ ሥልጣኑን ለመጠበቅ ባዋለደውና ስንከባከበው በቆየው የዘር ፖለቲካ ምክንያት በብሔረሰቦች መካከል የሰፈነው አለመተማመንና ጥላቻ መላ ሳይፈለግለት የሚቀጥል ከሆነ ተገኘ የተባለው እድገት ቀጣይነት ሊኖረው አይችልም። ኢኮኖሚያዊ እድገት ብቻ አገራቱን ከአመጽና ከብጥብጥ እንደማያድናቸው ብዙ ጊዜና በብዙ አገሮች ታይቷል። እጅግ በጣም ሊያሳስበን የሚገባው አሁንም ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ ብሔረሰብ ተከሉ የፌዴራል ሥርዓት በፈጠረው መከፋፈል ምክንያት ‹‹አገራችን ትበተን?›› እያልን የምንጠይቅ፣ እርስ በርስ ጦርነትና የዘር ፍጅት አደጋ የሚያሰጋን መሆናችን ነው! ከሃያ ሰባት  ዓመት በኋላ አሁንም አገራችን መንታ መንገድ ላይ ናት። ሊያሳስበን የሚገባው፣ ልንወያበት የሚገባው፣ መፍትሔ ልንሰጠው የሚገባን ወሳኝ ነጥብ ይህ ነው። ኢትዮጵያ – የትልቅ ሰው ምድረ በዳ  ኢትዮጵያችን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ናት። አገራችን ትልቅ ሰው አጥታለች። አገዛዙና በአገዛዙ ጉያ ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ታይቶ የማይታወቅ የቅንጦትና ድሎት ሕይወት እየመሩ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል ተብሎ በማይታሰብ ምቾት ላይ ይገኛሉ። የሕዝብ ችግር እንዳይመለከቱና የሕዝብ ብዞት እንዳይሰሙ ምቾቱና ድሎቱ ሕሊናቸውን ደፍኖታል። እንዲያውም የሕዝብ እሮሮ በጠመንጃ አፈሙዝ ይታፈናል ። በዚህም ምክንያት ወቅታዊ መብታቸውን የሚጠይቁትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ አሸባሪ፣ የአሸባሪ ደጋፊ ወዘተ.ዘግናኝ በደል የሚፈጸምባቸው፣ ያልተነገረላቸውና ስማቸው የማይታወቅ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሉ።ለእነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መጮህ መቻል አለብን።ከዚህም አልፈን ይህ ግፈኛ ሥርዓት ከዚህ የጥፋት አካሔዱ እጁን እንዲሰበስብ ትግል ከማድረግ ውጭ ምርጫ የለንም።

አገዛዙና የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን አበክረው የሚያወሩት ባለፉት ዓመታት ስለተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት ነው። ይሁን እንጂ፣ አገራችን ምን ያህል ትልቅ የኢኮኖሚ እድገት ብታስመዘግብ የፖለቲካው ሁኔታ እንደሚታየው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዘጋ ከሄደ፤  ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎች ሁሉ በጠላትነት ተፈርጀው በጥይት ሲደበደቡ እየታዘብን ነው። ድርጅቱ ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ ራሱን ወደ ሲቪል ድርጅትነት አለመለወጡ እጅግ የሚያሳስብ ብቻ  እንደሚታየው መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎች በጥይት እየተደበደቡ የሚቀጥሉ ከሆነ፤ እንደሚታየው አገዛዙ ሥልጣኑን ለመጠበቅ ባዋለደውና ስንከባከበው በቆየው የዘር ፖለቲካ ምክንያት በብሔረሰቦች መካከል የሰፈነው አለመተማመንና ጥላቻ መላ ሳይፈለግለት የሚቀጥል ከሆነ ተገኘ የተባለው እድገት ቀጣይነት ሊኖረው አይችልም። ኢኮኖሚያዊ እድገት ብቻ አገራቱን ከአመጽና ከብጥብጥ እንደማያድናቸው ብዙ ጊዜና በብዙ አገሮች ታይቷል። እጅግ በጣም ሊያሳስበን የሚገባው አሁንም ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ ብሔረሰብ ተከሉ የፌዴራል ሥርዓት በፈጠረው መከፋፈል ምክንያት ‹‹አገራችን ትበተን?›› እያልን የምንጠይቅ፣ እርስ በርስ ጦርነትና የዘር ፍጅት አደጋ የሚያሰጋን መሆናችን ነው! ከሃያ ሰባት  ዓመት በኋላ አሁንም አገራችን መንታ መንገድ ላይ ናት። ሊያሳስበን የሚገባው፣ ልንወያበት የሚገባው፣ መፍትሔ ልንሰጠው የሚገባን ወሳኝ ነጥብ ይህ ነው። ኢትዮጵያ – የትልቅ ሰው ምድረ በዳ  ኢትዮጵያችን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ናት። አገራችን ትልቅ ሰው አጥታለች። አገዛዙና በአገዛዙ ጉያ ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ታይቶ የማይታወቅ የቅንጦትና ድሎት ሕይወት እየመሩ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል ተብሎ በማይታሰብ ምቾት ላይ ይገኛሉ። የሕዝብ ችግር እንዳይመለከቱና የሕዝብ ብዞት እንዳይሰሙ ምቾቱና ድሎቱ ሕሊናቸውን ደፍኖታል። እንዲያውም የሕዝብ እሮሮ በጠመንጃ አፈሙዝ ይታፈናል ። በዚህም ምክንያት ወቅታዊ መብታቸውን የሚጠይቁትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ አሸባሪ፣ የአሸባሪ ደጋፊ ወዘተ. እያሉ ማሳደድና። መግደል ልማዳቸው ሆኗል። ተቃውሞ የሚያነሱ ዜጎች በጥይት ይደበደባሉ፤ በገፍ ይታሰራሉ፤ በዱላ ይቀጠቀጣሉ። ይህ ሁሉ ህይወት እንደቅጠል ሲረግፍ የወያኔ ባለስልጣኞች አንድም ቀን ብለው የተጎዱ ቤተሰቦችን አጽናንተው አሰከሬናቸው በክብር እንዲያርፍ አላደረጉም፡፡በሰው ሰራሽ አደጋ ለሞቱትም ጥፋተኞችን ለፍርድ ለመቅረብ ተንቀሳቅሰው አያውቁም።

በወያኔዎች ዘንድ ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚታወጀው እና ህዝቡ በግዳጅ እየወጣ የመንግስት አገልግሎች መስጫ ድርጅቶች ሳይቀሩ ለሁለት ሳምንተ ያልክ ተዘግተው ስራቸው ሀዘን ብቻ እንዲሆን መመሪያ የሚተላለፈው የስልጣን እና የጥቅም አጋራቸው ሲሞት እንጂ ሌላው ተራ ዜጋ እማ ሞቱን እንኩዋን የሚዘግበለት የሀገሩ የመገኛኛ ብዙሀን የለውም፡፡ ግብር የሚከፍልበት ቴሌቭዥን እንዲህ ያሉ ዜናዎችን ለህዝቡ እንዳያቀርቡ ጥርቅም አድርገው ይዘውታል፡፡የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ወያኔ ነው!ስለዚህ መፍትሄውም የችግሩን ምንጩ ከመሰረቱ ማድረቅ ነው፡፡ወያኔን ለማሰወገድ ደግሞ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሀዘናችንን አቁመን በልበ ሙሉነት ለዚህ ሀገራዊ ውርደት የዳረገንን አንባገነናዊ ስርዓት ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋን ይባርክ !!!

ኢትዬጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

ቴዎድሮስ ገዛኸኝ

ፀሀፊውን ለማግኘት teddygeza@yahoo.com ማግኘት ይቻላል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: