የዶክተር መረራ ከእስር መፈታት

ከአንድ ዓመት እስራት በኋላ ዛሬ  የተለቀቁት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ፣ ኦፌኮ፣ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ጠየቁ። ዶከተር መረራ እቤታቸዉ ሲደርሱ ዘመዶቻቸዉ እና በርካታ ደጋፊዎቻቸዉ ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

Merera-Gudina-Politics-court-hearing-source-VOA-Amharic-1

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ፣ኦፌኮ፣ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ከአንድ ዓመት በላይ እስር ላይ ከቆዩ በኋላ ዛሬ እቤታቸዉ እንደደረሱ በሰጡት መግለጫ በመፈታታቸዉ ቢደሰቱም የሌሎች መታሰር እንዳላስደሰታቸዉ እና እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።  ዶክተር መረራ ወደ መኖርያ ቤታቸዉ ከገቡ በኋላ ለህዝቡና ለፓርቲያቸዉ  መልክት አስተላልፈዋል።
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ተሾመ ዶክተር መረራ መፈታታቸዉ «እንደ ፓርቲ የኦሮሞ ትግል ዉጤት ነዉ» ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። የፓርቲዉ መሪ ዶክተር መረራ ቢፈቱም፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ወደ 500 የሚጠጉ የፓርቲው አባላት አሁንም  በእስር ላይ እንደiሚገኙም አቶ ሙላቱ ገልጸዋል።
ባለፈዉ ሰኞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ ከ528 ተጠርጣሪዎ ክሳቸዉ ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አስታዉቀዉ ነበር። በዚህም መሰረት ፣ ዶክተር መረራ ጨምሮ በፌዴራል ደረጃ 115 እስረኞች ዛሬ ተለቀዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሀመድ

DW

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: