አንዳርጋቸው ጽጌ የታገተበትን ሁለተኛ አመት ስናስታውስ ለነጻነት ትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት በማደስ ነው!!

Free-andargachew-tsigeየአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

የወያኔ አገዛዝ በአቡደራቡህ መንሱር ሃዲ ይመራ ከነበረው የየመን መንግሥት ጸጥታ ሃይል ጋር በመመሳጠር አንጋፋውን መሪያችንንና የትግል ጓዳችንን አንዳርጋቸው ጽጌን ከሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ አግቶ በቁጥጥሩ ስር ካስገባ እነሆ ዛሬ ሁለት አመት ሞላው።

የአለም አቀፉን ህግ በመተላለፍ ህወሃት ድንበር ተሻግሮና ባህር አቁርጦ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ሲያግት ቢያንስ ሁለት ውጤቶችን ለማግኘት አሰፍስፎ እንደነበር መገመት አያስቸግርም። አንደኛው ሥልጣን ላይ ተደላድሎ ለብዙ አመታት የመቆየት ምኞቱን አደጋ ላይ የጣለበትን የአርበኞች ግንቦት 7 እንቅስቃሴ አከርካሪ በመምታት ትግሉን አሽመደምደዋለሁ የሚል የተሳሳተ ስሌት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ህወሃትን የሚግደራደር ሃይል የትም ቢሆን ሊያመልጥ እንደማይችል በማሳየት የኢትዮጵያን ህዝብ አንገት ለማስደፋትና በፍርሃት አንቀጥቅጦ ለመግዛት የታለመ የእብሪት ውሳኔ ነው።

በዚህም ስሌት ህወሃት አንዳርጋቸው ጽጌን በእጁ ለማስገባት በአፈናው ተግባር ተባባሪ ለሆነው ለመንሱር ሃዲ መንግሥት ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካን Continue reading

Advertisements

በጋሚቤላ ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ጭፍጨፋ ተጠያቂው ወያኔ ነው!!! – የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nባለፈው ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው በመግባት በላሬና ጃካዋ ወረዳዎች በሚኖሩ የኑዌር ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ማካሄዳቸውን በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሚዲያዎች ጭምር ዘግበዋል።

ህወሃት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ በጋምቤላ ክልል ነዋሪ በሆኑ ወገኖቻችን ላይ እንዲህ አይነት የጅምላ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1996 የህወሃት ልዩ ጦር የተሳተፈበት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአኝዋክ ተወላጆች ላይ ተካሂዶ ከ400 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ተቀጥፎአል። በወቅቱ የፈደራል ጉዳዮች ሃላፊ የነበረው አባ ጸሃይና ሌሎች ቱባ ቱባ የመከላኪያና የደህንነት ባለሥልጣናት እጃቸው እንደነበረበት ቢታወቅም እስከዛሬ ድረስ አንዳቸውም ለፍርድ አልቀረቡም። ከ1996ቱ ጭፍጨፋ በተጨማሪም በክልሉ የሚካሄደውን የመሬት ቅሚያ የተቃወሙ፤ ከአያት ቅድሜ አያቶቻችው የወረሱትንና እትብታቸው ከተቀበረበት በሃይል አንፈናቀልም ያሉ Continue reading

ኢትዮጵያ፡ ተቃዎሞዎች ላይ የሚደረገው አፈና አልቀነሰም፡፡

ተቃዎሞ አድራጊዎች ላይ የሚፈጸመmው ግድያ እና እስር ለተከታታይ አራተኛ ወር ቀጥሏል፡፡

(ናይሮቢ፤.) – ከኖቬምበር ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በስፋት እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ተቃውሞ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል በጉልበት እያፈነው እንደሚገኝ ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ አስታወቀ፡፡ ከ2016 ዓ.ም.  መነሻ ጀምሮ በእየለቱ ሰዎች እንደሚገደሉ እና በዘፈቀደ እንደሚታሰሩ ሂውማን ራይትስ ወች አስታውቋል፡፡

የወታደራዊ ሰራዊትን ያካተተው የጸጥታ ሃይል ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ቀጥታ በመተኮስ ገድሏል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረው ያለምንም ክስ እንደታገቱ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተቃውሞው ድግግሞሽ የቀነሰ መስሎ ቢታይም አፈናው ግን ቀጥሏል፡፡

“ኦሮሚያን በበርካታ የጸጥታ ሃይሎች የማጥለቅለቅ እርምጃ የሚያመለክተው በተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ ባለስልጣን አካላቱ በከፍተኛ ሁኔታ አለመፈለጋቸውን ነው::” ብለዋል በሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌዝሊ ሌፍኮው፡፡ “መንግስት የፀጥታ ሃይሉን ሰብስቦ መመለስ ይኖርበታል፤ በስህተት የታገቱ ማንኛወንም ሰዎች መልቀቅ አለበት፤ አንዲሁም አላስፈላጊ ሃይል የተጠቀሙ የፖሊስ እና የወታደራዊ ሃይል አባላትን ተጠያቂ ማድረግ አለበት፡፡

ethiopia_presser_oromia_protest_1በጃንዋሪ 12 ቀን የአዲስ አበባ የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን መሰረዙን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር Continue reading

የቆሰለው አውሬ አገራችንን ይበልጥ ሳያቆስል በጊዜ እንነሳ!

12527915_780286462077576_1896452664_nየንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ለኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር ወያኔ የቆሰለ አውሬ ሆኗል ብለው ነበር። ፕ/ር ብርሃኑ በንግግራቸው፣ የቆሰለ አውሬ በህይወት ለመቆየት ሲል ያለ የሌለውን ሃይል በመጠቀም ጥቃት በሰነዘረበት ግለሰብ ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ወደ ሁዋላ የማይል በመሆኑ፣ ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበው ነበር። አውሬነት የጭካኔ ደረጃንና ሁዋላቀርነትን የሚያሳይ ገላጭ ቃል ነው፤ አውሬነት ወያኔ በህዝባችን ላይ ለሚፈጽመው ግፍ ጥሩ ወካይ ቃል ነው፤ ነገር ግን ወያኔ ከአውሬ አልፎ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፤ አደገኛነቱም ጨምሯል።

ፕ/ር ብርሃኑ በትክክል እንዳሉት የወያኔ የጥቃት ኢላማዎች ወያኔን የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ብቻ አይሆኑም። መላው የአገራችን ህዝብ በቆሰለው Continue reading

የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ Continue reading

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው

12527915_780286462077576_1896452664_nየወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላዩ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በእጅጉ ማሳስብ ጀምረዋል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ፣ እስራትና አፈና Continue reading

ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢ ትበል!!!

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በአማራ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ በሌሎችም ክልሎች ወገኖቻችን እየተገደሉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ታስረዋል። የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየቀጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሁላችንም ተሳትፎ የሚሻ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የገጠር ከተሞችን ሳይቀር ያዳረሰ መሆኑ የበርካታ ሕዝብ ስሜትንና ጥቅምን የሚነካ አጀንዳ በፍጥነት እንደሚሰራጭና ሕዝብን እንደሚያደራጅ አመላካች ነው። ከዚህ ሕዝባዊ ትግል በርካታ ድሎች Continue reading

%d bloggers like this: