የህዝባችን እንባ ለማቆም ሁላችንም አምርረን እንታገል !

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nኢትዮጵያ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት ተደቅኖባታል። ልጆቿ በያቅጣጫው ዋይታቸውን እያሰሙ ነው። የወያኔ የተበላሸ ስርዓት እና የስግብግብነት ተፈጥሮ ተደማምረው ህዝባችንን በቃላት ሊገለጽ በማይቻል ሰቆቃ ውስጥ ከተውታል። ህሊና ይዘው መፈጠራቸው ጥያቄ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ፣ ቅልብ የወያኔ ገዳይ ወታደሮች በኦሮሞ እናቶችና ህጻናት ላይ የፈጸሙት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በረጅሙ ታሪካችን ያላየነውና ያልሰማነው ነው። ባለፉት መንግስታት ለነጻነታቸው የጮሁ ወጣቶች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው ታሪክ የመዘገበው ሃቅ ነው፣ ነገር ግን ህጻናትና ታዳጊዎች እጅግ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ግንባራቸውንና ደረታቸውን በጥይት እየተመቱ ሲወድቁ ስንመለከት ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ ነው። አለም በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መወሰዱ ደግሞ የአገዛዙ ቁንጮዎችንና እነሱን ተከትለው ወደ ጥፋት አረንቋ የሚተሙትን ሁሉ ከሰው መፈጠራቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በአጋዚ ወታደሮችና በፌደራል ፖሊሶች በግፍ ለተነጠቀው ልጆቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ አልቅሷል፤ Continue reading

Advertisements

የሰላምን በር ጠርቅሞ የዘጋው ወያኔ ነው

12527915_780286462077576_1896452664_nየወያኔ አረመኔያዊ ያገዛዝ ስርዓት በህዝባችን ላይ የሚፈጽመው አፈና ግድያና ዝርፊያ በመጠኑም በዘግናኝነቱም ይበልጥ እያገጠጠ ስለመጣ ለወትሮው እንዳላዩ አይተው የሚያልፉትን ምዕራባውያን ለጋሾቹንና ወዳጆቹን ሳይቀር በእጅጉ ማሳስብ ጀምረዋል። ወያኔ ለምዕራባውያን ደህና ሎሌ በመሆን ወንጀሌን እንዳላዩ እንዲያዩልኝ ማድረግ እችላለሁ የሚለው አካሔዱ በውንብድና ተግባሩ ለከት የለሽነትና ዘግናኝነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ እየተሸረሸረበት ነው። ብዙዎቹ ምዕራባውያን ላለፉት ሁለት ወራት በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና አፈና ለማውገዝ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

አሜሪካንን ጨምሮ የወያኔ ለጋሽ ሀገራት የሆኑት ምዕራባውያን ሰሞኑን በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ የከፈተውን የዕብሪት ጭፍጨፋ፣ እስራትና አፈና Continue reading

ኢትዮጵያ አምባገነንነትን እንቢ ትበል!!!

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በአማራ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ በሌሎችም ክልሎች ወገኖቻችን እየተገደሉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተደብድበዋል፤ ታስረዋል። የህወሓት አገዛዝ ዜጎች መግደል፣ መደብደብና ማሰር መደበኛ ሥራው አድርጎታል።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየቀጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት እና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሁላችንም ተሳትፎ የሚሻ ነው። ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የገጠር ከተሞችን ሳይቀር ያዳረሰ መሆኑ የበርካታ ሕዝብ ስሜትንና ጥቅምን የሚነካ አጀንዳ በፍጥነት እንደሚሰራጭና ሕዝብን እንደሚያደራጅ አመላካች ነው። ከዚህ ሕዝባዊ ትግል በርካታ ድሎች Continue reading

ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ቢልም ተቃውሞ ግን ቀጥሎአል

12009571_452177654969272_2992392158665003976_n የኢህአዴግ አንድ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መተውን ባስታወቀ ማግስት በአምቦ፣ በአርሶ ኬፈሌና በሌሎችም የኦሮምያ ክፍሎች ተቃውሞው ቀጥሎአል።
በአምቦ የተካሄደው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ሰው መገደሉና በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። ከቆሰሉት መካከል ህጻናትም ይገኙበታል።
ከአምቦ ከተማ በተጨማሪ በ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሓ ከተማ ፣ በበደኖ፣ አርሲ፣ ሆድሮ ጉድሩና ሌሎችም ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
በሌላ በኩል ኦህዴድ ያወጣውን መግለጫ የኦፌኮው ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና አጣጥለውታል። ኦህዴድ ክልሉን የመምራት የሞራል ብቃት ስለሌለው ስልጣኑን ለህዝብ ያስረክብ ብለዋል።
ዶ/ር መረራ ፣ ዋናው ጥያቄ ” አዲስ አበባ ለምን ሰፋ አልሰፋ ሳይሆን፣ ለወደፊቱ አርሶደአሩ እንዳይፈናቀል ምን ዋስትና አለው” የሚለውን መመለሱ ላይ በመሆኑ፣ መግለጫው ይህንን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ይላሉ
በኦህዴድ የተሰጠው መግለጫ ተቃውሞውን ያስቆመዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር መረራ አይመስለኝም የሚል መልስ ሰጥተዋል። “ህዝቡ ይህ ድርጅት ወይም ያ ድርጅት Continue reading

ትግላችንን ተጠናክሮ በአንድነት ይቀጥል!

12373403_184095175272945_8742457289203482535_nየኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ በያቅጣጫው መነሳቱ የሚያኮራ ነው። ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን የመብት ትግል ጨምሮ በደቡብ፣ አማራ፣ አፋር፣ ጋምቤላና በሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የነጻነት ትግሎች ተካሂደዋል። አሁን በኦሮምያ እና በአማራ በተለይም በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የነጻነት ትግሎች የአጠቃላዩ የነጻነት ትግል አካሎች ናቸው። በእነዚህ የነጻነት ትግሎች ገዢው ፓርቲ ከህዝብ ጋር ለምንጊዜውም መለያየቱን ለማየት ችለናል። ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲልም፣ አቅሙ ቢፈቅድለትና ማግኘት ቢችል በምድር ላይ ያሉትን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ሁሉ በገዛ ህዝቡ ላይ ለመጠቀም ወደ ሁዋላ የማይል የአረመኔዎች ስብስብ መሆኑን አረጋግጠናል። በጭካኔውና በፍርሃቱ ብዛት የተነሳ በርካታ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ መብታቸውን በሰላም ለመጠየቅ ወደ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ተገድለዋል፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች በእስር ተንገላተዋል፤ በእስር ቤትም ማንነታቸውን ከማዋረድ ጀምሮ የተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች ተፈጽሞባቸዋል።

የኦሮሞ ህዝብ መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መነሳቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከያቅጣጫው ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው። ይህ ለነጻነት ሃይሎች ብስራት Continue reading

ወያኔ ሰራሽ የርስበርስ ግጭት ድግሶችን እናምክን

def-thumbየወያኔ ስርዓት የኢትዮጵያን አስተዳደር ሲያዋቅር በህዝብ ታሪካዊ አብሮነትና ተዛምዶ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብ ልዩነቶችን በማጉላትና ልዩነቱም የርስበርስ ጥርጣሬና ግጭት ምንጭ እንዲሆን በማድረግ ነው። ልዩነቱ የእርስ በርስ ግጭትና የረጅም ጊዜ ቁርሾ እንዲፈጥር ተደርጎ ከመዋቀሩ በተጨማሪ፣ ግጭቱ በማንኛውም ጊዜ እንዲነሳ ፖለቲካዊ ግፊት ይደረግበታል ። አንዱ ብሔረሰብ በሌላው ብሔረሰብ ክልል ውስጥ ሲሆን ባዕድነት እንዲሰማውና እንዲሰጋ፣ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ለማድረግ ላለፉት 24 አመታት ሲገፋ ቆይቷል፤ እየተገፋም ነው። በዘመነ ወያኔ በየቦታው በብሔር ወይም ብሔርሰብ ስም የተነሱ ግጭቶች በሙሉ የተቀሰቀሱት በራሱ በአገዛዙ ባለስልጣኖች እንጂ በህዝቡ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም። በተለያዩ የደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆችን ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ለማባረር የተወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ ባለስልጣኖቹ ከፊትና ከጀርባ ሆነው የቀሰቀሱዋቸው ፣ ያቀነባበሩዋቸውና የመሩዋቸው ለመሆናቸው ተጎጂዎች በግልጽ ሲናገሩ ሰምተናል።

በቅርቡ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለውና ተጥለው የተገኙት የአማራ ተወላጆች የሥርዓቱን ባህሪይ Continue reading

ለተከሰተው ረሀብ የሚደርስላቸው ተጠያቂውስ ማነው?

img_3839ቴዎድሮስ ገዛኸኝ

ዛሬም እንደገና የአገራችን ስም በድርቅና በረሃብ ምክንያት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መነጋገርያ ርዕስ ሆኖል፡፡ በዝናብ እጥረት ምክንያት በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የተከሰተው ድርቅና ረሃቡ  ዓለምን እያነጋገረ ቢሆንም  የድርቅ ውጤት የሆነውን ረሃብ አስቀድሞ ከመተንበይ ጀምሮ ዜጎችን ከሞትና ከስደት ከመከላከል አኳያ የኢህአዴግ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ከዓለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያን የሚመታው ድርቅና የምግብ እጥረት ችግር በየአስር አመታት ዑደት የመደጋገም ባሕርያት ይታይበታል።የነዚህ አስር አማታት ዑደት አገሪቱን ሲመታ የቆየው ረሀብ አንድና ተመሳሳይ መነሻ ያለው ነው። ይህም የአየር ንብረት መዛባት በአንዳንድ ቦታዎች ያስከተለው የዝናብ እጥረት ነው። ዘንድሮም ከ15 ሚልዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሕዝብ ለረሀብ መጋለጣቸውን የተለያዮ የአለም አቀፍ ሚድያዎች Continue reading

%d bloggers like this: